ንግድ ሚንስቴር በተያዘው ዓመት ለአገር ውስጥ ገበያ የቀረበው የስኳር መጠን ከአጠቃላይ የአገሪቱ ፍላጎት 10 በመቶን ብቻ እንደኾነ መናገሩን ካፒታል ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ስኳር ድርጅትም 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለገበያ ለማቅረብ አቅዶ፣ ማቅረብ የቻለው ግን ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በታች እንደኾነ መናገሩን ዘገባው አመላክቷል።
ሚንስቴሩ ይህንኑ የገለጸው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት እንደሆነ ተገልጧል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-11
