ሀገሬ ቲቪ

የተቀማው የባለሀብት መሬት

በደብረ ብርሃን ከተማ የ20 ባለሀብት መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደረገ፡፡ በባለሀብቱ ንብረት በሆነ በሊዝ ውል መሰረት ቅድመ ግባንታ ፣ግንባታ እና ማምረት መቼ እንዳለባቸው ገደብ ይቀመጣል፡፡ በከተማዋ በተሰጣቸው ጊዜ ወደ ስራ ያልገቡ ለ50 ለሚሆኑት ኢንቨስተሮች ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ 20 የሚሆኑት ደግሞ የተሰጣቸዉ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉን የደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ በከተማዋ ከ350 በላይ ኢንዱስትሪዎች ከ20 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል ተብሏል፡፡ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ከ70 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡ ከ80 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-12