ሀገሬ ቲቪ

የአስመጪና ላኪዎች የንግድ አገልግሎት ወደ ፌዴራል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መዘዋወሩ ተገለጸ።

የአስመጪና ላኪዎች የንግድ አገልግሎት ወደ ፌዴራል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መዘዋወሩ ተገለጸ።

በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪዎች የንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ፌዴራል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተዘዋውሯል።

ከዚህ በፊት ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪ የንግድ አገልግሎት አስተዳዳራዊ ክፍተቶች የታዩበት የኮንትሮባንድ ንግድ የተበራከተበት መሆኑን ተከትሎ ወደ ፌደራል ተዛውሯል።

የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ማንኛውም አስመጪና ላኪ ነጋዴ ወደ ተቋሙ በአካል መቅረብ ሳይጠበቅበት ሲስተሙን በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ተጠቁሟል።

የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኩል ይሰጥ እንደንበረ ይታወሳል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-07-11