
የሱዳን ግጭት ወደ ለየለት ጦርነት እንዳያመራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከነገ በስቲያ ወደ ለየለት ጦርነት ለመግባት አፋፍላይ ባለችው ሱዳን ጉዳይ በግብፅ እንደሚመክር ይጠበቃል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 12 ሳምንታትን ያስቆጠረው የሱዳን ግጭት ሀገሪቱን ወደ ለየለት ጦርነት ለመክተት ከአፋፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በቻድ የሱዳን ድንበር የሰብዓዊ ቀውስ በሱዳናውያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አስታውቋል።
በወንድማገኝ አበበ
2023-07-11