ሀገሬ ቲቪ

የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ መስማማታቸውን የወታደራዊ ህብረት ሃላፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።

የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ስዊድን ኔቶን ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ መስማማታቸውን የወታደራዊ ህብረት ሃላፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።

የቱርክ መሪ የስዊድንን ጥያቄ ወደ አንካራ ወስደው ለፓርላማ እንደሚያቀርቡ እና "ለማፅደቅ እንደሚጥሩም ቃል ገብተዋል።

ለጉዳዩ ምላሽ የሰጡት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን እና ቱርክ ጋር በዩሮ-አትላንቲክ አካባቢ ለመጠበቅ እና መከላከልን ለማጎልበት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስተርሰን እና ስዊድን እንደ 32ኛ የኔቶ አጋርነት ለመቀበል እጓጓለሁም ብለዋል ጆ ባይደን። አብዛኛዎቹ የኔቶ አባል ሀገራት የስዊድን አባልነት ቢድግፉም ሀገሪቱ መቼ አባል እንደምትሆን የተቆረጠ ቀን አለመቀመጡ የኔቶ ዋና አዛዥ ተናግረዋል።

በናርዶስ ታምራት
2023-07-11