ሀገሬ ቲቪ

ከደረጃ በታች በሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ለደረጃ የወጡ መስፈርቶችን ያላሟሉ እና ከደረጃ በታች የሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች የተዘጉ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 7፣ አቃቂ ቃሊት 2፣ በቦሌ 2 እና በኮልፌ ቃራኒዮ 2 ትመህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ትምህርት ቤቶቹ ለ2016 ዓ.ም ማስተማር የማይችሉ መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ የተማሪዎችን ውጤት የሚገልጽ መረጃ ለተማሪዎችና እውቅና ፍቃድ ለሰጣቸው አካል እንዲያስረክቡ አሳስቧል፡፡

በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-07-13