ሀገሬ ቲቪ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እና ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ እና ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከተጀመረ ከ13ኛ ሳምንቱን ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነትን በሚያበቃበት እንዲሁም በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየታቸው ነው የተነገረው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በሱዳን ጉዳይ በሚመክረው የካይሮ ስብሰባ ለመታደም ግብጽ ይገኛሉ፡፡

ትናንት ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማምሻውን ግብጽ የገቡት ዶ/ር ዐብይ የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቤተመንግስታቸው አቀባበል እንዳደረጉላቸው የግብፅ መገናኛ ብዙኃን አስታውቀዋል።

ግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ምክንያት እስካሁን ድረስ መግባባት ላይ ሳይደርሱ መቆየታቸው ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2023-07-13