ሀገሬ ቲቪ

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባላ ሀገራት በትናንትናው ዕለት ባጠናቀቁት ስብሰባቸው ቻይና በእስያ ፓስፊክ አካባቢ እያደርገችው ያለ እንቅስቃሴ አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጥስ እና በአካባቢው ስጋት እየፈጠረ ነው የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባላ ሀገራት በትናንትናው ዕለት ባጠናቀቁት ስብሰባቸው ቻይና በእስያ ፓስፊክ አካባቢ እያደርገችው ያለ እንቅስቃሴ አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጥስ እና በአካባቢው ስጋት እየፈጠረ ነው የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

ታዲያ ይህ የኔቶ ውሳኔ የቢጂንግን እድገት ለመግታት እና ቻይና ለምዕራባዊያን ተገዥ እንድትሆን ለማድረግ የተጠነሰሰ ሃሳብ ነው ስትል ቻይና ውድቅ አድርገዋልች።

የኔቶ አባል ሀገራትም ሆኑ ማንኘውም አካል በቻይና ሉዓላዊነት ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ ቻይና አስጠንቅቃለች።

ይህን አልፎ የቻይናን ህጋዊ መብትና ጥቅም የሚያደፈርስ ማንኛውም አካል ካለ የከፋ ምላሽ እንደሚጥብቀው አስታውቃለች።

በናርዶስ ታምራት
2023-07-13