ሀገሬ ቲቪ

በፀረ ሙስና ንቅናቄ 7 ቢሊየን ብር ከምዝበራ መታደግ መቻሉ ተገለፀ።

በፀረ ሙስና ንቅናቄ 7 ቢሊየን ብር ከምዝበራ መታደግ መቻሉ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶላ በከተማው ያሉ ወጣቶችን፣ የሃይማኖት ተቋማትንና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰራ ስራ መሆኑን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ 3 ሺህ 811 የሙስና ጥቆማ ቀርበዋል።

በሙስና ተግባር ውስጥ የተሳተፉ 2 ሺህ 751 አካላት ተጠያቂ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በሲዳማ ክልል በገጠር አካባቢዎች በተለያዩ አካላት የተመዘበረ 59 ሺህ 482 ሄክታር መሬት እንዲሁም በከተሞች 16 ሺህ 856 ካሬ ሜትር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል።

በማህሌት አማረ
2023-07-13