የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ተሻግሯል። በዚህ ጊዜ ታዲያ ቫይረሱ ድርሽ ያላለባት አንድ ሀገር አለች ሰሜን ኮሪያ። አሁን ላይ ግን የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ መመዝገቡ የሀገሪቱ ብዙኃን መገናኛ አስታውቋል። በዋና ከተማዋ ፕዮንግያን ትኩሳት ካለበት ታካሚ የተወሰደ የናሙና ምርመራ ከ ኦሚክሮን ቫይርስ ምልክት ጋር ተቀራራቢ ሆኖ መገኘቱ ድንጋጤን ፍጥሯል። ምንም ዓይነት የኮቪድ 19 ክትባት የማትጠቀመው ሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ የወረርሽኝ ስርጭት እንዳይከሰት ተሰግቷል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ቻይና እና ሩሲያ ክትባት እንኪ ቢሏትም ሰሜን ኮሪያ ክትባቱን እናንተ ተጠቀሙ እኔ አያስፈልገኝም ማለቷን የፍራንስ 24 ዘገባ ያሳያል የሀገሪቱ መንግሥት ቫይረሱ ሳይዛመት በፍጥነት ለመቆጣጠር እንዲቻል አስቸኳይ አዋጅ አውጇል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-05-12
