ሀገሬ ቲቪ

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያቸው እንዳፈናቀለ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው ድርቅ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያቸው እንዳፈናቀለ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

እንደ ተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት በሶማሊያ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች፣ በኢትዮጵያ 516,000 ሰዎች እንዲሁም በኬንያ 466,000 ሰዎች በድርቅ ተፈናቅለዋል ብሏል።

የአፍሪካ ቀንድ ከ2020 መገባደጃ ጀምሮ ተደጋጋሚ ድርቅ ገጥሞታል።

በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ድርቅ 23.4 ሚልዮን ሰዎች የምግብ እጥረትና 5.1 ሚልዮን ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደገጠማቸው ሪፖርቱ አስታወሷል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-07-17