የቻይና ኮንትራክተሮች በኢትዮጵያ የጀመሯቸውን ፕሮጀክቶች እያቋረጡ መሆኑ ተነገረ፡፡
ኮንትራክተሮቹ ኢትዮጵያ ከውጭ አበዳሪዎች የጠየቀችውን የዕዳ ማዋቀር በመዘግየቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የያዟቸውን ፕሮጀክቶች በማቋረጥ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ መንገድ አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር የትምጌታ አሥራት የቻይናው ኮንትራክተር ክፍያውን የጠየቀው በዶላር ሲሆን መንግሥት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር ስላበት ይህንን ማድረግ ባለመቻሉ ክፍያውን መፈጸም የሚችለው በብር ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-17
