ሀገሬ ቲቪ

አዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ

ከ20 ዓመት በላይ በሥራ ላይ የቆየው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን ይተካል ተብሎ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በአዲሱ ዓመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ ቀደም ተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከታቸውን የተለያዩ የንግድ ዘርፎች በማካተት የተዘጋጀ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ አይገባም ተብለው ይጠቀሱ የነበሩ አንዳንድ የንግድ ዓይነቶች ጭምር የተካተቱበት ነው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከእረፍት መልስ በአዲሱ የስራ ዘመን ያፀድቃቸዋል ተብሎ ከሚጠበቁ ጉዳዮች መካከል የመጀመሪያው ሊሆን እንደሚችል ሪፖርተር ዘግቧል።

በማህሌት አማረ
2023-07-18