የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎትብ 897 ሺህ ጉዳዮችን በማስተናገድ ከ1 ነጥብ 77 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ በ2015 በጀት ዓመት ስኬታማ ስራ መስራቱንም ተናግሯል፡፡
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች 897 ሺህ 71 ጉዳዮች ላይ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችን አስታናግጃለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡
በዚህም 1 ነጥብ 77 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ መቻሉን ገልጿል።
1 ሺህ 733 ሃሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጉን እና ከተያዙት ሃሰተኛ ማስረጃዎች ውስጥ 87 በመቶዎቹ የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያዎች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-07-18
