ግዙፍ ህንጻዎች እና መሰረተ ልማቶች ያላቸው ከተሞች የመሬት ስር የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚያጋጥማቸው ተገለፀ።
በቺካጎ አሜሪካ የተደረገ ጥናት ግዙፍ ህንጻዎች እና መሰረተ ልማቶች ከእግራችን ስር ያለው መሬት እንዲሞቅ በማድረግ የመሬት ስር የአየር ንብረት መለወጥን እንደሚያስከትሉ ጠቁሟል።
ይሄው የመሬት ስር የአየር ንብረት ለውጥ እንደከባቢ አየር ንብረት ለውጥ ሳይሆን በመሬት ስር ያለ ሌላ አደጋን ሊያስከትል የሚችል ሁነት መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።
የከርሰ ምድር ውሃ መበከልን እና በመሬት ስር ያሉ እንደባቡር ጣቢያ ያሉ ተገልጋዮች በከፍተኛ ሙቀት እንዲታመሙ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል በመግለፅ ጉዳዩ ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልገው አስታውቀዋል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-07-18
