የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም የሚካሄደውን 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔውን ጀመረ።
በጉባዔው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዪ የክልላችንን ብሎም የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በስንዴ ልማት፣ በእርሻ ሜካናይዜሽን እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ እና በትምህርቱ ዘርፍ በከፍተኛ ንቅናቄ የተሠራበት ዓመት እንደነበርም ገልጸዋል።
የማዳበሪያ እጥረት የወለደው የሕገወጦች መበራከት በክልሉ አርሶ አደሮች በኩል ቅሬታን የፈጠረ መኾኑን የገለጹት አፈ ጉባዔዋ ለጉዳዩ ዘላቂ እልባት ለመስጠት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው በርካታ ጉዳዮች መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በይስሐቅ አበበ
2023-07-19
