ሀገሬ ቲቪ

ኪሳራ የገጠመው አፕል

አፕል በቴክኖሎጂ አክሲዮኖች ሽያጭ ውስጥ በዓለም ላይ እጅግ ውድ የሆነ ኩባንያነቱን ማጣቱ ተሰማ። የሳውዲ አረቢያ የነዳጅ እና ጋዝ አምራች ”አራምኮ” ከሁለት ዓመት ገደማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአይፎን ከፍተኛውን ቦታ አግኝቷል።
ከ 2020 ጀምሮ አራምኮ የመጀመሪያውን ቦታ ሲይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ። በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት የድፍድፍ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በመጨመሩ የኢነርጂ አምራቾች ድርሻ አይሏል።
ኪሳራው ከአንድ አመት በፊት ኩባንያው ካስመዘገበው ዓመታዊ ትርፍ ጋር ለየ ቅል ሆኗል ሲል ብሉምበርግ አውርቷል። የዓለማችን ትልቁ እና በጣም የታወቀው ዲጂታል ምንዛሬ ክሪፕቶ ከረንሲ ፈረንጆቹ አምና ባሉት 2021 ከፍተኛ ሪከርድ ካስመዘገበ ወዲህ ኩባንያው 60 በመቶ ያህል ዋጋውን አጥቷል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-05-12