ወደ ውጭ ገበያ ከተላከ ቡና 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ240 ሺህ 369 ቶን በላይ ቡና ወደ ውጪ ገበያ ተልኮ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ360 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ በመላክ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
ገቢው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቅናሽ ማሳየቱ ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-19
