ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት ወጪ ቆጣቢ አሠራርን በመከተሌ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ችያለሁ አለ።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት ወጪ ቆጣቢ አሠራርን በመከተሌ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ችያለሁ አለ።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ አጠቃላይ የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈፃጸም ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው ይህን የተናገሩት።

ስራ አስፈፃሚዋ ይህ የገንዘብ ቁጠባ የእቅዳችንን 106% ያሳካንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ለሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ሳፋሪኮም ከሚያቀርበው የመሰረተ ልማት ኪራይ 758 ሚሊዮን ብር እንዳገኘም በመግለጫው አስታውቋል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-07-19