ሀገሬ ቲቪ

በኢትዮጵያ የለጋሽ አካላት ድጋፍ መቀነስ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ተግዳሮት ፈጥሯል ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የለጋሽ አካላት ድጋፍ መቀነስ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ተግዳሮት ፈጥሯል ተባለ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ወጪ በአብዛኛው በለጋሽ አካላት የሚሸፈን መሆኑን አንስተው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የለጋሽ አካላት ድጋፍ በተለያየ ምክንያት እየቀነሰ በመምጣቱ ጠቁመዋል፡፡

ይህም በሥራው ላይ ጫና መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱን እየፈለጉ ተደራሽ ያልሆኑ 22 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች መኖራቸውን ሚኒስትሯ ጨምረው አንስተዋል፡፡

ሚኒስትራ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የ36 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የበጀት ስምምነት በመንግሥት እና በአጋር ድርጅቶች መካከል በተፈረመበት ወቅት ነው፡፡

በይስሐቅ አበበ
2023-07-19