
የኮቪድ ቫይረስ ከቻይናው ዩውሃን ቤተሚከራ ሊያፈተልክ ይችላል የሚል መላምት ላይ ጥናት ያደረጉት የኩዊኒፒያክ እና የዩጎቭ ዩኒቨርሲቲዎች መላምቱ ትክክል ነው ብለዋል።
የዩንቨርስቲዎቹ ጥናት እንዳመላከተው ከሆነ በቤተሙከራ ውስጥ የሚሰሩት ተመራማሪዎች በቂ የሆነ የደህንነት መጠበቂያ በሌለበት ከአደገኛ ቫይረሶች ጋር እየተጋፈጡ ምርምሩን ያደርጋሉ፤ በዚህም ሳቢያ የቻይና መንግስት ቫይረሱ ላደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በተደረገ ጥናት ከ64 እስከ 66 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን ለኮቪድ ቫይረስ መከሰት ተጠያቂዋ ቻይና እንደሆነች እንደሚያምኑ ጠቁሞ ነበር።
የአሜሪካው ኮንግረስም ሳርስ የተባለው የኮቪድ ዝርያ የመጣው ከዚያው ቤተሙከራ ባፈተለከ ቫይረስ ሳቢያ ነው ብሎ ነበር።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-20