በትግራይ ክልል ወርቅን ጨምሮ በማዕድን ፍለጋና ማምረት ላይ ተሰማርተው የነበሩ ኩባንያዎችን ስራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።
በክልሉ በማዕድን ዘርፉ ልማትና የፍለጋ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ስራቸውን ማካሄድ ተቸግረው መቆየታቸውን የሚታወስ ነው።
አሁን ላይ በትግራይ ክልል ወርቅ፣ ሲሚንቶና ሌሎች የማዕድን ማምረትና ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠረላቸው መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቴዎስ ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በክልሉ የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አስቀድሞ ስራ መጀመሩ መጀመሩ የሚታወስ ነው።
በማህሌት አማረ
2023-07-20
