ሀገሬ ቲቪ

በኡጋንዳ 25 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች በድንበርና በኤርፖርት ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

በኡጋንዳ 25 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች በድንበርና በኤርፖርት ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

በኡጋንዳ የተያዙት እነዚህ ሰዎች ምንም አይነት ህጋዊ የጉዞ ሰነድ እንደሌላቸው መገለፁን ዘኦብዘርቨር ዘግቧል።

የኡጋንዳ ባለስልናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢቴንቤ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል የውጭ ዜዎች ዝውውር እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።

እነዚህ ሰዎች መዳረሻቸው የት እንደሆነም አብዘሃኞቹ እንደማያውቁ ተነግሯል፡፡

እንደ ካምፓላ፣ ማሳካ፣ ምባራራ፣ ምባሌ፣ ፎርት ፖርታል ባሉ የኡጋንዳ ከተሞች ውስጥ በህገወጥ ደላሎች ተታለው የሚመጡ በርካታ ስደተኞች መኖራቸው ተገልጿል።

በሳምሶን ገድሉ
2023-07-20