በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የክልሉ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ የክልሉን ወቅታዊ ጉዳይ አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ኃላፊው በመግለጫቸው በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑን አጋጥሞ የነበረው አለመረጋጋት በፀጥታ ኃይሎት የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር እየዋለ ስለምሆኑ ጠቁመዋል።
አጋጥሞ በነበረው የፀጥታ ችግር በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱም ባሻገር ለነዋሪዎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት ችግሩ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተሰማርተው አንጻራዊ ሰላም በማስፈን ላይ መሆናቸውን አቶ ኡገቱ አስረድተዋል።
በይስሐቅ አበበ
2023-07-20
