ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በስልክ ተወያዩ።
በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪ በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ለማምጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ገጻቸው ገለጸዋል።
ሩሲያ የዩክሬን የእህል ምርቶችን ለማጓጓዝ ወደ ጥቁር ባሕር ወደቦች የሚገቡ መርከቦች የወታደራዊ ጥቃት ኢላማ ላደርጋቸው እችላለሁ በማለት ማስጠንቀቋን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አብራርተዋል።
ዘለንስኪ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለመነጋገር የሚያስችል መድረክ እንዲመቻችም ጠይቀዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር በፀጥታ፣ በዲጂታላይዜሽን መስኮች የሁለትዮሽ ግንኙነት የመመሥረት ፍላጎት እንዳላቸው ዘለንስኪ ገልፀዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2023-07-21
