የ2016 በጀት ዓመት በጀመረ 12 ቀናት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ 52 ሺህ 129 አገልግሎቶች በኦንላይን መሰጠታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ይህ አገልግሎት የተሰጠው በ2016 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ጀምሮ ባለፉት 12 ቀናት ብቻ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ሚኒስቴሩ በ2015 በጀት ዓመት 1 ሚሊዮን 496 ሺህ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎቶች መሰጠታቸውን ተናግሯል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኦንላይን አገልግሎቶችን ወደ 90 ከመቶ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በብሩክታዊት አሥራት
2023-07-21
