ሀገሬ ቲቪ

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድጋፍ

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የእንሳት መኖ ድጋፍ አደረገ። ኮሚቴው ምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ ኩምቢ ለሚገኙ 5ሺህ አባወራዎች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል።

የእንሣት መኖ ስርጭቱ በዋናነት በአካባቢው ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ መሆኑን ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።በመኖ ድጋፉ እስከ 150 ሺህ እንስሳት ይመገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኮሚቴው ከዚህ ቀደም በአፋር ክልል ሲልሳ ለሚገኙ 9 ሺህ የተፈናቀሉ ሰዎች እንደ ሶላር የእጅ ባትሪዎችን፣ ጀሪካኖችን፣ የማዕድ ቤት እቃዎችን፣ ምንጣፍ ያሉ መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችንእና መጠለያ ድጋፍ አድርጓል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-05-12