ሀገሬ ቲቪ

በ2016 ዓ.ም የወረቀት መታወቂያ አይሰጥም ተባለ።

በ2016 ዓ.ም የወረቀት መታወቂያ አይሰጥም ተባለ።

ቤት ለቤት የጤና እክል ላለባቸው ከሚሰጠው አገልግሎት ውጪ ሁሉም ነዋሪ ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ቀደም ሲል ለመታወቂያ፣ ልደት፣ ሞትና መሰል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሲሰጥባቸው የነበሩትን ካርዶች ሙሉ ለሙሉ መቀየሩን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ‹‹ሲኩሪቲ ፕሪንተር›› የተባለና ከአሜሪካን ሀገር የተገዛው ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያም የመጀመሪያው ፕሪንተር ነው ብለውታል፡፡

አገልግሎት ላይ ያልዋሉትን ጨምሮ 25 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱት ካርዶች መወገዳቸውንና እነዚህን የሚተካ ህትመት ታትሞ መሰራጨቱን ገልፀዋል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-07-21