በ2015 በጀት ዓመት መንግሥት ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች 16 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ከድጎማ ሥርዓቱ 180 ሺህ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
መንግሥት ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ባደረገው ድጎማ የባለሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ እስከ ሀገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የተጀመረው የድጎማ ስርዓት በ2016 በጀት ዓመትም የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።
በማህሌት አማረ
2023-07-24
