የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ የተመደቡበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከትናንት ጀምሮ መግባት ጀምረዋል፡፡
የመውለጃ ቀናቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ሴት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት እንደ መደበኛ ተፈታኝ መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ሆኖም ለመፈተን የወሰኑ ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
በናርዶስ ታምራት
2023-07-24
