በገንዘብ አያይዝ እና አጠቃቀም የነበረው ክፍተት ለዋጋ ንረቱ መባባስ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
ለዚህም በአዲሱ በጀት ዓመት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ትኩረት አደርጎ እንደሚሰራ ተናግሯል።
የብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት የዋጋ ንረቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተ ቢሆንም በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የነዳጅ፣ የምግብ እንዲሁም ከማዳበሪያ ዋጋ ጋር ተያይዞ ያለው ከፍተኛ ጫማሪ ምጣኔውን እንደጨመረው ጠቁመዋል።
ያለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥ በማሳለፏ ምክንያት ተጀምረው የነበሩ የለውጥ ሥራዎች በትኩረት እንዳይሠሩ አድርጓል ብለዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2023-07-25
