ሀገሬ ቲቪ

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የንግዱን ማህበረሰብ የሚያስፈራሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የንግዱን ማህበረሰብ የሚያስፈራሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

አንዳንድ ግለሰቦች ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚጠበቅባቸውን የዜግነት ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ፤ ሀሰተኛ የማደናገሪያ ና ማስፈራሪያ ስልቶችን በመጠቀም የንግዱን ማህበረሰብ በማሸበር ጥቅም የማጋበስ ዝንባሌ እንደሚታይ አገልግሎቱ ጠቁሟል፡፡

ስለሆነም የንግዱን ማህበረሰብ በማስፈራራት በወንጀል ድርጊት ለመጠቀም የሚሞክሩ ግለሰቦችን ከተመለከቱ ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በስልክ ቁጥር 011-812-8261 በመጠቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ያለ አግባብ ለመጠቀም በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦችም ከወንጀል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-07-25