ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 90 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 90 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ19 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚኖረው ተነግሯል።

ይህ የተባለው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው፡፡

ተቋሙ ከዚህ በተጨማሪ 92 ሚሊዮን ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ የመገንባት እቅድ መያዙንም አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲኖር የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋሙ እንደሚሰራም ስራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል፡፡

በሞባይል ኔትዎርክ ማስፋፊያ የተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር 92 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡

የንግድ ስርዐትን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ ጀምሮ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ህይወትን የሚያቀል አገልግሎቶች ወደ ገበያ እንደሚመጡም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የተጠቃሚዎችን ፍላጐት ለማርካት በ3ጂ ፣ 4ጂ እና 5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ የሞባይል ደንበኛን የማስተናገድ አቅምን 92 ሚሊየን ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75 ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2023-07-27