ሩሲያ ኤርትራን ጨምሮ ለ6 የአፍሪካ አገራት የምግብ ስንዴ በነጻ እንደምትለግስ ቃል ገብታለች።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በሩሲያና አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው ይህን ያስታወቁት።
ስንዴውን በነጻ የሚያገኙት ኤርትራ፣ ሱማሊያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ናቸው።
ፕሬዝዳንቱ ሩሲያ በቀጣዮቹ አራት ወራት ለስድስቱ አገራት የምትለግሰው የስንዴ መጠን ከ25 እስከ 50 ሺህ ቶን ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-28
