ሀገሬ ቲቪ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ አሳሰበ።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ አሳሰበ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ የገበያ ጥናት በማድረግ በሚያዝያ ወር ላይ ወቅታዊ የማድረግ ስራ መሰራቱ ተነግሯል።

በዚህም መሰረት እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸው የነበሩ ሰዎች እስካሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ከሚጠበቀው አንጻር በርካቶች ገና ናቸው ተብሏል፡፡

በአዲሱ ጥናት መሰረት ለመኖሪያ ቤት 50 በመቶ እንዲሁም ለድርጅት 75 በመቶ እንዲከፍሉ መወሰኑን ይታወሳል፡።

በጥናቱ መሰረትም 800 ሺህ የሚጠጋ ግብር ከፋይ የሚጠበቅ ሲሆን በአዲሱ ስሌት መሰረት እስካሁን 223 ሺህ ግብር ከፋዮች ብቻ መክፈላቸው ተነግሯል።

በህጉ መሰረትም ከተቀመጠው ጊዜ ውጭ የሚመጡ ግብር ከፋዮች ባልተከፈለው ግብር መጠን 5 በመቶ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

በቤት ወይም በከተማ ቦታ ኪራይ እና የቤት ግብር አዋጅ መሰረት የጣራ እና ግድግዳ የግብር ክፍያ ሲተገበር መቆየቱ ይታወሳል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-02