ሀገሬ ቲቪ

በ2015 በጀት ዓመት ወደ ዉጭ ከተላኩ ማዕድናት 226.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ወደ ዉጭ ከተላኩ ማዕድናት 226.8 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህ የተነገረው የማዕድን ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

በሪፖርቱ የተመላከተ በማዕድን ዘርፉ ያለዉ ኮንትሮባንድና ሌብነት ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትርዶ/ር ፍጹም ከህገ-ወጥነት ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን በህግና በአሰራር ለመፍታት ይሰራል ነዉ ብለዋል፡፡

በማዕድናት ወጪ ምርት ላይ ስብጥርን ማስጠበቅ እንደሚገባም ሚኒስቴሯ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የድንጋይ ከሰል አገራዊ ምርትን በማሳደግ ሙሉ በሙሉ ከዉጭ የሚገባዉን ለመተካት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-03