ሀገሬ ቲቪ

በ2015 በጀት ዓመት ከ252 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና ማግኘታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

በ2015 በጀት ዓመት ከ252 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና ማግኘታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

ይህ የተነገረው የኘላንና ልማት ሚኒስቴር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱን የተጠናቀቀውን (የ2015) በጀት ዓመት አፈፃፀምን ሲገመግም ነው፡፡

በግምገማው የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በተልዕኮና በትኩረት መስክ እንደገና ለማደራጀት በተጠናው ጥናት መሰረትም ከ99 ፖሊ-ቴክኒኮች መካከል 76ቱ ወደ ሥራ መግባታቸው ተጠቅሷል።

ምቹ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎች ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በሀገር ውስጥ ከ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ የዕቅዱን 95 ነጥብ 45 በመቶ ማከናወን መቻሉም ተጠቅሷል።

የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው መካከልም 36 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።

ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት በበጀት ዓመቱ ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑ ተጠቁሞ ከዉጭ ሃገር የሥራ ስምሪት አኳያ ደግሞ የፓስፖርት ጉዳይ ትልቁ ችግር መሆኑ ተነግሯል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-03