በ2015 በጀት ዓመት ከውጭ ሀገር ጎብኚዎች ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ ገቢ የተገኘው ከ900 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው ነው፡፡
ከቱሪስት መዳረሻ መሠረተ ልማት፣ ከአገልግሎት ጥራትና ከዓለም አቀፍ የንግድ ትስስሮች የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በበጀት ዓመቱ የተሻለ እንደነበር ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በኮቪድ እና በሰላም ዕጦት ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ ስብሰባና ክብረ በዓላትን ጨምሮ የጀመሩበት ወቅት በመሆኑ በበጀት ዓመቱ 20 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ዜጎች የቱሪስት እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ተነግሯል።
በኮቪድ ጊዜ የአውሮፕላን በረራዎች የተሰረዙበት፣ ሆቴሎችና የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተዘገቡት፤ ዓለም አቀፍ የሰዎች እንቅስቃሴም የተገታበት በመሆኑና በጦርነቱ ወቅት ደግሞ የውጭ ሚዲያው ሲሰራ የነበረው ዘመቻ እንዲሁም በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመጎብኘት አስቸጋሪ የነበረ በመሆኑ የቱሪዝም ዘርፉ ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በናርዶስ ታምራት
2023-08-03
