ሀገሬ ቲቪ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል እየተስተዋሉ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገልፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል እየተስተዋሉ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገልፁ፡፡

አቶ ደመቀ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን በትናንትናው እለት አስታውቀዋል፡፡

ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች እንዲመለሱ እና ችግሮችን ለመፍታት ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ መንግሥት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ወረራና የንፁኃን ግድያ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስባለው ሲሉ ገለጸዋል።

በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭጥ እንዲያቆም የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያሳድሩ ጠይቀዋል።

በወንድማገኝ አበበ
0202-08-03