ሀገሬ ቲቪ

በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ የሚመራ ልዑክ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለመመልከት ሱማሌላንድ ሀርጌሳ ገብቷል።

በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ የሚመራ ልዑክ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ለመመልከት ሱማሌላንድ ሀርጌሳ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ የበርበራ ወደብን ለኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ ተጨማሪ አማራጭ ለማድረግ የሚያስችለውን ውይይት ከሚመለከታቸው የሶማሌላንድ ባለስልጣናት ጋር አድርጓል።

በውይይቱም ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የወጪና ገቢ ንግድ ፍላጎቷን ለማሟላት በርበራ ወደብን መጠቀም በምትችልባቸው መንገዶች ላይ ምክክር ተደርጓል።

ኢትዮጵያ ለገቢና ወጪ ንግዷ ከምትጠቀምበት የጅቡቲ ወደብ በተጨማሪ የወደብ አማራጭ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-08-03