ሀገሬ ቲቪ

20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናዊያን ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናዊያን ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ድርጀቱ እንዳለው በሱዳን ከሶስት ወር ተኩል ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሀገራቸውን ጥለው ሸሽተዋል፤ አሁንም በመሸሽ ላይ ይገኛሉ።

የሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ 2 በመቶ ይህሉ አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት ውስጥ እንደሚግኝም ተግልጿል። ለዚህም አፋጣኝ የምግብ ድጋፍ እንዲደርግ ተመድ ጥሪ አቅርቧል።

በሱዳን የሚካሄደውን ጦርነት ሸሽተው የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 930 ሺህ የሚጠጋ ሲሆን በሀገሪቱ የተፈናቀሉት ደግሞ ከ3 ሚሊየን በላይ መሆናቸውን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የቅርብ ጊዜ ዘገባ አመልክቷል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-08-03