ሀገሬ ቲቪ

ናይጄሪያ ለኒጀር የምታቀrበውን የኤሌትሪክ ኃይል አቋርጣለች።

ናይጄሪያ ለኒጀር የምታቀrበውን የኤሌትሪክ ኃይል አቋርጣለች።

በናይጄሪያ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢ ኩባንያን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ እንደዘገበው በኒጀር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ከናይጄሪያ ወደ ኒጀር የሚጓዘው ከፍተኛ የኤሌትሪክ መስመር ተቋርጧል ብሏል።

በኒጀር በርካታ አካባቢዎች ለኃይል መቆራረጥ የተዳረጉ ሲሆን በአገሪቱ ከተከሰተው መፈንቅለ መንግሥት ጋር ተያይዞ ሁኔታውን እንዳያባብሰው ተሰግቷል።

የናይጄያው ኩባንያ በኒጀር ብቸኛው የኤሌክትሪክ አቅራቢ ነበር።

ኒጀር ከጎረቤቷ ናይጄሪያ የኃይል ጥገኝነት ራሷን ነፃ ለማድረግ የኃይል ማመንጫ ግድቦችን እየሰራች ትገኛለች።

በወንድማገኝ አበበ
2023-08-03