ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላልይበላ እና ጎንደር የሚያደርገውን በረራ አቋርጧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላልይበላ እና ጎንደር የሚያደርገውን በረራ አቋርጧል።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል በተፈጠረ እና እየተስፋፋ የመጣውን ግጭት ተከትሎ በክልሉ አለመረጋጋት ተከስቷል።

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አሸናፊ ዘርዓይ "ወደ ጎንደር እና ላልይበላ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸውን ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ምንጭ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ይህን ይናገሩ እንጂ በረራዎች የተሰረዙበትን ምክንያት እንደማያውቁ ገለፀዋል።

በተመሳሳይ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ስፔን፣ ፖላንድ እና ሌሎች ሀገራት ዜጎቻቸው ወደ አማራ ክልል እንዳይሔዱ አሳስበዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-08-04