ሀገሬ ቲቪ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ውሳኔ አሳልፈ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ውሳኔ አሳልፈ፡፡

ምክር ቤቱ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ባጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

በመደበኛ የህግ ስርዓት መሰረት የትጥቅ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህገ መንግስቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን አስታውቋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-04