የ አዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብኒ ቱሪዝም ቢሮ ከግንቦት 5 እስከ 7 ለሚያዘጋጀው 13ተኛው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኅላፊ አቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሀት ቢሮው በየዓመቱ መዲናችን አዲስ አበባን የሚያሳዩ የኪነጥበብ ሥራዎች መስራቱን አንስተው ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ ከተማ አቀፍ ፌስቲቫል በርካታ የኪነጥበብ ሥራዎችን የያዘ ነው ብለዋል።
"በስነጥበባት ኀብራዊ መልክ የተዋበች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በጊዮን ሆቴል የሚከበረው 13ኛው የኪነጥበብ ፌስቲቫል ኪነጥበብ ሀገርንና የሀገርን ሁለንተና አጉልተው ሲያሳዩ መቆየታቸውን በተግባር ማሳየት የዚህ ፌስቲቫል ቀዳሚ ዐላማ ነው ተብሏል።
የዘንድሮው የኪነጥበብ ፌስቲቫል በርካታ የ ሥነጥበብ ሙያዎችን ያቀፈ ከመሆኑም በላይ ቲያትር ቤቶችን፣ ወረዳዎች እና ክፍለ ከተሞችን በ 14 ዘርፎች አወዳድሮ እንደሚሸልም አቶ ሰርፀ ፍሬ ስብሀት ተናግረዋል ።
‘’በሥነጥበባት ኀብረብሔራዊ መልክ የተዋበች ኢትዮጵያ’’ በሚል መሪቃል ከግንቦት 5 - 7 በግዮን ሆቴል የተዘጋጀውን ፌስቲቫል የከተማዋ ማኀበረሰብ በመታደም ኪነጥበብን እንዲያበረታታ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-05-12
