አይ.አር.ሲ (IRC) የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋምቤላ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሚያገለግል የመድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
ድርጅቱ ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከ13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለግሷል።
በኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ማኳይ እና ለጎግና ጋምቤላ ወረዳዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት ድጋፍ አድርጓል።
በተጨማሪ በጋምቤላ ከተማ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሚያገለግሉ መድኃኒቶችና ለኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ የሚረዱ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በማኀበራዊ ገጹ አስታውቋል።
በክረምት የሚከሰቱ አደጋዎችና ወረረሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገውልናል ሲሉ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ጫኔ ሁሴን ተናግረዋል።
በወንድማገኝ አበበ
2023-08-09
