ሀገሬ ቲቪ

በዘንድሮ ዓመት ከ68 ሺ መዝገቦች በላይ በፍርድ ቤት ወሳኔ ተሰጥቶባቸዋል

በ2015 በጀት ዓመት አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተባቸዉ 172 ሺህ 940 መዝገቦች ከ68 ሺህ መዝገቦች በላይ በፍርድ ቤት ወሳኔ እንደተሰጠባቸዉ የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በበጀት ዓመቱ እንደአገር በአቃቤ ህግ እጅ 198 ሺህ 434 የምርመራ መዝገቦች እንደነበሩ ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

ከእነዚህ መዝገቦች መካከል 188 ሺህ 875 ምርመራ ማጣራቱን በሪፖርቱ አመላክቷል።

ምርመራ ከተደረገባቸዉ 172 ሺህ 340 መዝገቦች መካከል 68 ሺህ 42 መዝገቦች ፍርድ ቤት ቀርበዉ ዉሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

64 ሺህ 624 በሚሆኑት መዝገቦች ላይ ደግሞ ተከራክሮ ጥፋተኛ ማስባሉንና የቅጣት ዉሳኔ ማሰጠቱን ገልጿል።

የተጠርጣሪዎች እና ምስክሮች አለመቅረብ ፍትህ እንዲዘገይ ማድረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪ መዝገቦች ተከሳሾች ባልተገኙበት እንዲወሰን እያስገደደ ያለ ተግዳሮት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-08-09