በበልግ እርሻ ከ25 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት መገኘቱ ተነገረ፡፡
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በ2015/16 ምርት ዘመን በመኸር እርሻ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ሐረሪ ክልሎችና እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ16 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የታረሰ ሲሆን 75 በመቶ የሚሆነው በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በበልግ እርሻ ከ2 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት በዘር የተሸነፈ ሲሆን እስካሁን ድረስም ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ሄክታር ሰብል ተሰብስቦ ከ25 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት መገኘቱም ተገልጿል።
በናርዶስ ታምራት
2023-08-09
