ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ ከተማ በሞተር ብስክሌት ላይ የተጣለው ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሞተር ብስክሌት ላይ የተጣለው ገደብ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እሰኪነሳ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አስታውቋል፡፡

ይህንን መልዕክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እወስዳለሁም ብሏል፡፡

ቢሮው የሞተር ብስክሌት ማሽከርከርን እስከ እሮብ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ማገዱ የሚታወስ ነው፡፡

በማህሌት አማረ
2023-08-09