ሀገሬ ቲቪ

በ2015 በጀት ዓመት ከዕድል ጨዋታዎች 507 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ።

በ2015 በጀት ዓመት ከዕድል ጨዋታዎች 507 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከዕድል ጨዋታዎች በጠቅላላ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም አስታውቋል፡፡

የተገኘው የተጣራ ትርፍ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2 ነጥብ 78 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን የአስተዳደሩ ጠቅላላ ገቢ ደግሞ የ328 ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡

አስተዳደሩ ለዕጣ ዕድለኛ ደንበኞቹ ከ420 ሚሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ገልጿል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-08-15